News Detail
Dec 14, 2020
707 views
የሴቶች ትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡- ትምህርት ሚኒስቴር
የሴቶች ትምህርት ተሳትፎ ከዚህ በፊት ከነበረው ይበልጥ ለማሳደግ ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ አስታውቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ነቢል መህዲ በአሁኑ ጊዜ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ እንደ ሀገር ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከማምጣት ባሻገር በትምህርት ገበታቸው እንዲቆዩና ለውጤት እንዲበቁ አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን እና የትምህርት ተቋማት ለሴት ተማሪዎች ምቹና ከትንኮሳ የፀዱ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የሺሐረግ ነጋሽ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ
ወሲባዊ፣ አካላዊና ስነ ልቦናዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶችን ለመቅረፍ ሁሉም ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ዘርፍ የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የሃይል ጥቃቶች እንዲሁም ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚያጠነጥን ሰነድ ቀርቦ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡