News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 08, 2020 793 views

የትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በሰላም ማስከበር ዘመቻ ላይ ለተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት የ10ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የትምህርት መርሀግብሩን ለማስቀጠል የሀገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዮስ መስሪያ ቤቱ የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የትምህርት ሚኒስትርም እንደ ተቋም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ የ10ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን እና በቀጣይም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም አስታውቀል።
የገንዘብ ስጦታውን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ ትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ከዚህ ቀደም "ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ደም መለገሳቸው ይታወሳል።
Recent News
Follow Us