News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 23, 2020 499 views

30 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጀምረዋል። - የትምህርት ሚኒስቴር

ከአዲስ አበባ ከተማ እና አጎራባች ዞኖች ውጭ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብዓት ያሟሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጀምረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ( ፒ ኤች ዲ) ትምህርት ቤቶቹ ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉት ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር ጀምረዋል ብለዋል።

በዚህም በመላ ሀገሪቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያሟሉ 30 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ትምህርት መጀመራቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል ።

በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን ግብዓት ሲያሟሉ እንደሚከፈቱም ተነግሯል።

ቀሪ ትምህርት ቤቶችም በየአካባቢው በተቋቋመው ኮሚቴዎች አማካኝነት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸው ተገምግሞ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንደሚገቡም ተገልጿል።

ባለፈው አንድ ሳምንት 1/3ኛ የሚሆን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለትምህርት ቤቶች የተሰራጨ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማዳረስ እየተሠራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

Recent News
Follow Us