News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 09, 2020 628 views

የመገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ለሚዲያ ባለሙያዎች፣ ለክልል ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነቶች፣ ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎችና ለሚኒሚዲያ ተወካዮች በትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠ ነው።

  ባለሙያዎቹ የኮቪድ 19ኝ ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት በሚስራው ስራ ውስጥ ማህበረሰቡ በቂ እውቀት እንዲኖረው በማድረግ ትልቅ        ኋላፊነት   አለባቸው ተብሏል።

 የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃረጓ ማሞ የመገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈት የበኩላቸውን ኃላፊነት   እንዲወጡ   አሳስበዋል።

 ቀድመው ትምህርት የጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ተሞክሮ ለሌሎች በማከፈል ህብረተሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልክ የንቅናቄ ስራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

 የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጡ መመሪያዎችን ለህብረተሰቡ በማሳወቅ ተግባራዊ እንዲያደርደርጉ በማስቻል   ሙያዊ   ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል።

በመድረኩ የየክልሎቹ የህዝብ ግንኙነት ባላሙያዎች የየክልላቸውን ትምህርት ቤቶች ዝግጅት ተሞክሮን እያቀረቡ ነው።

Recent News
Follow Us