News Detail
Oct 13, 2025
22 views
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትረው ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣የማህበረሰብ ጉድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተካሂዷል፡፡
በዚሁ ጊዜ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች ወደ ገበያ ሲገቡ commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትሪው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ፈጠራና ተቋማቱ በቅንጅትና በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የየራሳቸውን የንግድ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ማበልጸጊያ (incubation centers) ማዕከላት ያላቋቋሙ ተቋማት በአፋጣኝ አቋቁመው ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰራዊት ሀንዲሶ(ዶ/ር) ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ውጤቶችን የመጨረሻ ግብ የምርምር ውጤቶቻቸውን ወደ ገበያ ገብተው የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱና ገቢ የሚያስገኙላቸው መሆኑን አንሰተዋል፡፡
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ውጤቶችን ማሳተም የመጨረሻ ግብ አድርገው ከመቁጠር ልማዳዊ አሠራር ወጥተው የሀገርን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚያፋጥኑ አዳዲስ ፈጠራዎችን ማፍለቅ የሚያስችሉ ውጤታማ ምርምሮችን እንዲያካሄዱ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማዊ ትሥሥርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ሀላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማህበረሰቡንና የኢንዱስትሪውን ችግር ለመፍታት የሚያካሄዱት የምርምር ውጤቶች ወደ ገበያ ገብተው ለተቋሙም ሆነ ለተመራማሪዎች ገቢ ከማስገኘታቸው በተጨማሪ ምርምሮች መጠናከር አቅም ከመሆናቸውም በተጨማሪ የምርምር ሂደቱ ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣የማህበረሰብ ግድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ ምርምሮች የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈቱ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጻኦ ያደርጋልም ተብሏል።