News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 13, 2025 27 views

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበሰውን ብሄራዊ የሠንደቅ አላማ ቀንን አክብረዋል፡፡
በክበረ-በዓሉ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያና መሠባሠቢያ መሆኑ አንስተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሀገራችንን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ከፍታ አስጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ በዚህ ትውልድ ላይ የተጣለ መሆኑን አመላክተዋል።
አንደ ትምህርት ዘርፍም የምንቀርጻቸውና የምናስተገብራቸው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣መመሪያዎችና ደንቦች በእውቀትና ክህሎት የዳበሩ፤ ስብእናቸው በተሟላ መልኩ የተገነቡ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ እና ለዚህም ጠንክሮ መስራት ከትምህርት ዘርፉ ተዋንያኖች የሚጠበቅ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።
ሰንደቅ አላማችን ፈተናዎችን ተጋግዞ በመሻገር የአደገች ሀገር ለመገንባት አቅማችንን አሟጠን ርብርብ ለማድረግ መሰባሰቢያ ይሆነና ብለዋል።
Recent News
Follow Us