News Detail
Oct 20, 2025
40 views
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘገጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በተዘጋጃ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡
በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድና ተዛማጅ ጉዳዬች ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ባጋሩት ሀሳብ እየተቀየረ ያለውን የዓለም ጂኦፓለቲክስ ቀድሞ በመረዳት የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ አካሄድና ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝግጁነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ብሄራዊ ጥቅሞች ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ልዩነቶቾን በማጉላት መደነቃቀፍን የሚፈጥሩ አጀንዳዎች፣አመለካከቶችና ሌሎች ፈተናዎችን በማስወገድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
ሀገር ያለ ብሔራዊ ጥቅም ልትቀጥል እንደማትችል አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በጥልቀት መረዳት እንደሚገባም አብራርተዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋና ዋና ፈተናዎች ጂኦስትራቴጂያዊ ጉዳዮችና እና መልከዓ ምድራዊ የሆኑ ተግዳሮቶች እንደሆኑ አመላክተው እነዚህን ተግዳሮቶች ለመሻገር ዓለም አቀፋዊ ሕጎችን መሠረት በማድረግ ብሔራዊ ጥቅምን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የተፈጥሮ ሀብት፣ የህዝብ ብዛት፣ ጅኦፖለቲካዊ አቀማመጥ እና የተደራጀ ተቋማዊ አቅምን አስተሳስረን ተለዋዋጭ በሆነው የዓለማችን ሁኔታ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ተግቶ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ያለህዝብ ተሳትፎ በመንግሥት ብቻ መሰልና ወሳኝ የሆኑ ብሄራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅም ይሁን ማሳካት የማይችል መሆኑን በመጥቀስ ህዝቡ ከማንነቱ፣ ከህልውናውና ከነገ ተስፋው ጋር የተሳሰረውን ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም ጆኦስትራቴጂካዊ ቁመና ጉዳይ ላይ በትኩረት ሊመለከተውና ሊሠራበት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በቀረበው ሀገራዊ ሠነድ ላይ ከትምህርት ዘርፉ ሰራተኞች ምን ይጠበቃል በሚለው ጉዳይ ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።