News Detail
Apr 05, 2025
137 views
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመሩ ሁሉ አቀፍ የሪፎርም ስራዎች በተቀናጀ የህዝብ ግንኙነት ስራ ሊደገፉ እንደሚገባ ተገለጸ፤ የዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ይገኛል።
በትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች የሪፎሮም ስራዎችን በህዝብ ግንኙነት ስራ በማጀብ ለማህበረሰቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እውቀት የሚገበይባቸውና ሀሳብ በነጻነት የሚራመድባቸው ተቋማት መሆናቸውንም ገልጸዋል።
አክለውም በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራት ተደራሽነት፣ተገቢነት እና ፍትሃዊነት የማረጋገጥ ስራዎችን በህዝብ ግንኙነት ስራ ማጀብ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ቦጋለ ከዚሁ ጋር አያይዘው እንደገለጹት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሃላፊዎች ሙያቸውን በሚገባ አውቀው የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ አበርክቶ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸው የትምህርት ሚኒስቴርም በማንኛውም ጊዜ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢንጅነር ቦጋለ ገ/ማርያም በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ፎረም መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ ግንኙነትን ለማጠናከርና ተሞክሮዎችን ለመቀመር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የፎረሙ ተሳታፊዎች በዩኒቨርስቲው በሚኖራቸው ቆይታ መልካም ተሞክሮዎቹን እንደሚያጋሩና ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ጠንካራ ልምዶችን እንዲቀስሙ እድል እንደሚፈጥርላቸው ጠቅሰዋል፤
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) በበኩላቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ከጊዜ ወደ ጊዜ በቴክኖሎጂ እየተራቀቀ በመምጣቱ ይህን የተረዳና ከጊዜው ጋር የሚራመድ ኮሙኒኬሽን መተግበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Recent News
የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ብቃት ማዕቀፍ ለትግበራ መሆኑ ተገለጸ፤
Mar 14, 2025
የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፤
Mar 14, 2025