News Detail
Sep 09, 2024
5.5K views
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ለአገር አቀፍ ፈተና ከተቀመጡ 674,823 ተማሪዎች ውስጥ 36, 409 ወይም 5.4 በመቶ የማለፊያው ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ9,114 ተማሪዎች ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።
በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 28,158 ወይም 9 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ 8,251 ወይም 2 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አመላክተዋል።
በፈተናው 1,221 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በባለፈው ዓመት ከተመዘገበው 220 አንጻር የተሻለ ውጤት መሆኑም ተገልጿል። ቀደም ሲል በነበረው የመሰናዶ ትምህርት በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ከትግራይ ቀላሚኖ ት/ቤት አንድ ተማሪ 675 ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ፈተናቸውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዲስ አበባ አግዚሊየም ካቴድራል ት/ቤት 575 (በሴት ተማሪ) በማህበራዊ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ 538 (በሴት ተማሪ) ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ።
በዚህ ዓመት ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ከአምናው በተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ 1,363 ት/ቤቶች ግን ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በመጨረሻም 50 በመቶና በላይ ያመጡት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ጠቅሰው የተወሰኑ ተማሪዎችም በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
Recent News
Oct 08, 2024
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል።
Oct 08, 2024
የሬሚዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
Oct 08, 2024
Sep 10, 2024
Sep 17, 2024
Sep 04, 2024