News Detail
Aug 30, 2024
1.1K views
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ “ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባዔው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉባኤው በትምህርት ሴክተሩ አንድ አይነት አረዳድ እንዲኖርና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የትምህርት ሴክተሩ ምን እንዲሆን ነው የምንፈልገው የሚለው ላይ የጠራ አመለካከት መያዝ እንደሚገባም አንስተዋል።
አክለውም በትምህርት ሴክተሩ ከታች ጀምሮ የሚሰሩ ሥራዎች ታማኝነትና ሀቀኝነት( honesty and integrity )፣ ሚዛናዊነትን (fairness) ፣ ጥራትን(Quality) እና ኃላፊነትን( responsibility ) የተላበሱ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ አንስተው ይህንን ማድረግ ከተቻለ መጪውን ጊዜ ማስቀጠል የሚችሉ ትውልዶችን መፍጠር እንደሚቻልም አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ለዕድሜ ልክ ስኬት የሀገራዊ የትምህርት ስርዓቱ ጥራት ወሳኝ መሆኑን አንስተው ለወደፊት ስኬቶች ዘር የሚዘሩባቸው ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በትምህር ለትውልድ የተገኙ ልምዶችን በመወሰድ ችግሮችን ለመፍታት ሁላችንም በሚገባን ልክ ተሰናስለን የትምህርት ሥርዓቱን መምራት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጉባኤው ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰው ሃብት ስምሪትና ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት፣ የክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ እና አጋር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024