News Detail
Jul 09, 2024
959 views
ጠንካራ የጥናትና ምርምር የአስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የጥናትና ምርምር አስተዳደራዊ የአሰራር ስርዓቶችን በማጠናከርና በመገንባት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲና Ohio State University ጋር በመተባበር ለሁሉም የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ስልጠና እየሠጠ ነው።
ስልጠናው በምርምር ተቋማት ውስጥ ጠንካራ የጥናትና ምርምር አስተዳደራዊ ስርዓት መዘርጋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
በመርሃ ግብሩበ ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ቁልፍ መልእክት ያስተላለፍት የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ስርጸት ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥናትና ምርምር ስነ ምግባር ጥሰቶችና ያልተገቡ ልምዶችን ጠንካራ የአስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዶ/ር ሠራዊት አያይዘው እንደገለጹት ጥናትና ምርምር በማድረግ ሂደት ውስጥ ተመራማሪዎች በቅድሚያ የጥናትና ምርምር መርሆች፣ህጎችና ደንቦችን በሚገባ መረዳት፣ ማክበርና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ካልቸራል ጉዳዬች ሀላፊ ሪያን ብሬደን በበኩላቸው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ጠንካራ የጥናትና ምርምር አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የተቋማቱን ተወዳዳሪነት ማሣደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሀላፊው አያይዘው እንደገለጹት ጠንካራ የአስተዳር ስርዓት የተቋማቱን የውስጥ አቅም ለማጎልበትና ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገር የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያግዝ አብራርተዋል።
የተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች በበኩላቸው ጠንካራ የጥናትና ምርምር አስተዳር በማስፈን ረገድ ያሉ ማነቆችን አንስተው ውይይት አድረገዋል።
በዚህም በጥናትና ምርምር እንዲሁም ሀብት በማፈላለግና በማመንጨት የሚሳተፉ ምሁራንን የሚያበረታታና የሚደግፍ የአሠራር ስርዓት መዘርጋት ተመራማሪዎችን በስራ ገበታቸው እንዲቆዩና እንዲተጉ የሚያግዝ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024