News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jul 10, 2024 1.4K views

ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈታናን አስጀመሩ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በአብርሆት ቤተ-መጽሃፍት በመገኘት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሄራዊ ፈተናን አስጀምረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት እየተተገበረ ያለው የወረቀትና የኦን ላይን ፈተና (hybrid exam) መሆኑን አመልክተዋል። ለወደፊቱ ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን መፈተን ሲቻል የበለጠ ፈተናውን ከስርቆትና ከመኮራረጅ ከመታደጉም በላይ ለትምህርት ጥራት የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል ብለዋል።
በተጨማሪም ፈተናውን ለማስተዳደር፣ ለቁጥጥር፣ ለህትመት፣ ለማጓጓዝ፣ ለሴኩዩሪቲ እና መሰል ወጭዎችን ለመቀነስ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በመጨረሻም የፈተናውን ድባብ ለማበላሸት ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ስለሚንሸራሸሩ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበው ተማሪዎችም ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ መክረዋል።
Recent News
Follow Us