News Detail
Jan 30, 2023
4K views
"የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን ያመላከተ ነው" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ጥር 22/2025ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ2014ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተና የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ገልጸዋል።
የዚህ አመት የፈተና ውጤት አንድምታም ለዓመታት ሲንከባለል የቆየ በርካታ ችግሮች መገለጫ እና ተሸፋፍኖ የቆየውን እውነተኛ የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተሰጠው ፈተና ስርቆትን እና ኩረጃን ማስቀረት የተቻለበት እንደሆነ ገልፀው ውጤቱም የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።
በተገኘው ውጤት መሰረትም ከ 50 በመቶ በታች ያመጣ ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንደማይገባም ተናግረዋል።
በ2014 ዓ.ም በተሰጠው ፈተና በሁለቱም የትምህርት መስክ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ 29 ሺህ 909 የሚሆኑት ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ማስመዝገባቸው ተገልጿል።
በመሆኑም በቀጣይ እንደሀገር በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉም አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024