News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 21, 2022 3.5K views

"በ2014 ዓም በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለጥያቄዎቻችን አፈጣኝ ምላሽ በመስጠት ላደረጉልን ድጋፍ እናመስግናለን" ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ፣የትምህርት ሚኒስትር

31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የፀጥታ አካላትን፣የትምህርት ቢሮዎች ፣ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች በሂደቱ አበርክቶ ለነበራቸውን ተቋማት የምስጋና እና የእውቅና የመስ
በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ በፈተና ዝግጅትና ሂደቱ ወቅት አበርክቶ ለነበራቸው የጸጥታ አካላት፣የክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮዎች፣ዩኒቨርሲቲዎች ፣ፈታኝ መምህራን እና አጠቃላይ ለፈተና አስፈጻሚዎች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ወቅት ለጥያቄዎቻችን አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላደረጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።
በሌላ በኩል የትምህርትና ፈተናዎች ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ርብርብና የተቀናጀ ስራ የፈተና ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ እንደተቻለ በመግለጽ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በፈተና አሠጣጥ ሂደቱ ወቅት አበርክቶ ለነበራቸው ተቋሟት የእውቅና ሠርተፍኬት ተሰጥቷል።
Recent News
Follow Us