News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 21, 2022 3.7K views

"ሀገርን ለማዳን የተከፈለውን መሥዋትነት የትምህርት ሥርዓቱን በማሻሻል መድገም ይገባናል" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) 31 የትምህርት ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በመልክታቸውም ሀገርን ለማዳን የተከፈለውን መሥዋዕትነት የትምህርት ስርዓቱን ስብራቶች በማሻሻል መድገም ይገባል ብለዋል።
በሀገራችን የገጠመንን ችግር መፍታት የምንችለው በትምህርት ላይ በሚሠራው ሥራ መሆኑን የገለጹት ሚኒሥትሩ ይህንን በመረዳት ሁሉም ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
በመሆኑንም የአንድ ቢሮ ኃላፊ ወይም ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ኅላፊነት ብቁና ጥሩ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል ሥራ መሥራት መሆኑን አውቆ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
አክለውሞ የትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን በተናጥል በሚደረግ ጥረት መፍታት አይቻልም ያሉ ሲሆን ለዚህም ሁሉም በሚችለው ልክ ዘርፉን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲመክር የቆየ ሲሆን የትምህርት ጥራትን ለማረገገጥ እና ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል መፍራት በሚቻላቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ደርሷል።
በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማሣተፍ ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢን በመፍጠር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ ተገልጿል።
በተከታታይ ሦስት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 31ኛው የትምህርት ጉባኤ በተሳታፊዎች ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
Recent News
Follow Us