News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 09, 2022 3K views

በሁሉም አማራጭ የዜጎችን የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ።

የትምህርት ሚኒስቴር" ሀገር አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ቀን " የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለማህበረሰብ የተፋጠነ እድገት በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በስነስርዓቱ መክፈቻ ላይ እንዳሉት ሀገርን መለወጥ የሚቻለው በትምህርት ላይ ለውጥ ማምጣት ሲሰጡ ብቻ ነው።
በመሆኑም በጎልማሶች ትምህርት ማንበብ መጻፍ እና ማስላት የማስቻል ግብ እንዲሳካ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ለዘርፉ ትኩረተ እንዲሰጡና እንዲደግፉ ዶ/ር ፋንታ ጥሪ አቅርበዋል።
በጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም በእድሜያቸው ትምህርት ቤት ያልገቡትን ወጣቶችና ህጻናት በማቀፍና በማበረታታት የመደበኛ ትምህርትን መደገፍ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራሞ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሴፍ አበራ በበኩላቸው የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት ይሰጥ እንደነበረ ተናግረዋል።
የተለያዩ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ከገበያ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
''የጎልማሶችና' መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለማህበረሰብ የተፋጠነ እድገት'' በሚል ርዕስ እየተከበረ ባለው በዚሁ በዓል ላይ ልዩ ልዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
Recent News
Follow Us