News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 09, 2022 3K views

ዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው::

ጥቅምት 25/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው::
በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለምአቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት መካከል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ስምምነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ምጥጥን እና የአካቶ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል::
በስምምነት ፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መሰል ተቋማት ወደ ሀገራችን መምጣታቸው የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር ሚናቸው ጎላ መሆኑን ገልጸዋል::
ሚንስትር ዴኤታዉ አክለውም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል::
በትምህርቱ ዘርፍ አለም አቀፍ አጋርነትና ትብብርን በማጠናከር አካዳሚያዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲዊ አቅምን ማጠናከር እና መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል::
የዓለምአቀፉ ትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ መንሱር ቢን ሙሳላም በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረሙት ሥምምነት በትምህርቱ ዘርፍ አለም አቀፍ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም እና ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ የአሁኑን እና የመጪውን ትውልድ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል::
Recent News
Follow Us