News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 13, 2022 2.6K views

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ፈተናውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።
ተፈታኞችም ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ወደ ዩኒቨርስቲው እየገቡ ይገኛሉ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ዩኒቨርስቲው ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያደረገውን ዝግጅት እና አቀባበል ተመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ9 ካምፓሶቹ ከ38 ሺህ በላይ ተፈታኞቹን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
#ምስጋና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
Recent News
Follow Us