News Detail
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሁል ጊዜ ተግባር አድርጎ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
በዳግማዊዊ ሚኒሊክ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት በተከናወነው የበጎ ፈቃድ አልግሎት መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ሁላችንም የሁል ጊዜ ተግባር በማድረግ ቀጣይነት ባለው መልኩ መፈፀም እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ከሌሎች ጋር አብሮ በመኖር የምናከናውናቸው ብቻ ሳይሆን ለራሳችንም የምንሠራቸው መልካም ተግባራት መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀን መርሃ ግብር በት/ቤት ውስጥ መሆኑ ተማሪዎች ይህንን አገልግሎት እንደ ባህል ይዘው እንዲያድጉ ለማድረግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር ) በበኩላቸው ትምህርት ቤቶችን ንጹህ፣ ማራኪና ምቹ ለማድረግ ባለፈው ዓመት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀን የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
በዳግማዊ ምኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት የትምህርት፣ ጤና ሚንስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሰራተኛች እንዲሁም የዳግማዊ ሚኒልክ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች እና የትምህርቱ ማህበረሰብ የአካባቢ ጽዳት እና የችግኞችን የመንከባከብ ስራ ሰርተዋል።
ለትምህርት ቤቱም የትምህርት ስራ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች በትምህርት ሚኒስቴር ተበርክቷል፡፡ ፡