News Detail
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከፊላንድ አምባሳደር ሆሎፔነን ኦቲ ጋር ተወያዩ።
የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ላይ ባለመድረሱ ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚጠይቅ የጠቀሱት ሚኒስትሩ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ እና ደረጃውን በጠበቀ ዲዛይን ለመገንባት እንደታቀደና በዲዛይኑ ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያም ገለፃ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ የፊንላድ አምባሳደር ሆሎፔነን ኦቲ በበኩላቸው አገራቸው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በመዘርጋቷ የትምህርት ጥራት እንዲኖርና የትምህርት ስርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ እገዛ እንዳደረገ ገልፀዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረጉ የሁለትዮሽ ትብብር ስራዎች በዋናነት የትምህርት ፍትሃዊነት እና አካታችነት ትኩረት የሚሰጥባቸው ተግባራት ሲሆኑ የመምህራን ስልጠናን እንደሚያካትትም አብራርተዋል።
የትምህርት ቤቶች ምገባን ለማጠናከርና ለአደጋ ጊዜ ትምህርት ፕሮግራም የሚውል 3 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በቀጣይ በቅርብ በሚዘጋጀው የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ሰነድ ላይ የትምህርት ዘርፉ የጥራት ሪፎርም ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ተብሏል።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026