News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Aug 17, 2020 1.3K views

የተማሪዎች ነፃ ዝውውር ውሳኔ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ያለመ ነው:- ትምህርት ሚኒስቴር

በትምህርት ሚኒስቴር የ ተላላፈው ከ 8ኛና 12ኛ ክፍል ውጪ ያሉ ተማሪዋች ነፃ ዝውውር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት መሆኑ ተገለፀ ።

በትምህርት ሚኒስቴር የ ተላላፈው ከ 8ኛና 12ኛ ክፍል ውጪ ያሉ ተማሪዋች ነፃ ዝውውር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት መሆኑ ተገለፀ ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ ውሳኔው በኮሮና ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የትምህርት መርሃ ግብር ሲጀመር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት እና ወረርሽኙ የፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የታሰበ ነው ብለዋል።በአሁን ሰዓት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ያለነው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይም ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት ከተመለሱ በኋላ የትምህርት ጥራቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የትምህርት ጥራቱን በዘላቂነት ለመፍታትም በ 2014 ዓ.ም ወደ ተግባር የሚገባ አዲስ ስርዓተ ትምህርት እየተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል ።

በነፃ ዝውውር የተዘዋወሩ ተማሪዋች የትምህርት ምዕራፉ ሲጀመር በተዘዋወሩበት የትምህርት ክፍል ባለፈው የትምህርት ምዕራፍ ላይ ማካካሻ ወስደው ቀጣዪን የትምህርት መርሃ ግብር የሚቀጥሉ ይሆናል።

በኮሮና ወረርሽኝ ምክኒያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ከ 26 ሚሊየን በላይ ተማሪዋች ከ ትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዋች ውጪ የነፃ ዝውውር ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።

Recent News
Follow Us