News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jun 19, 2020 1K views

የትምህርት ሚኒስቴር ለአቅመ ደካሞች እና ጧሪ ለሌላቸው 200 አባ ወራዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19ኛን ተጽዕኖ ለመቋቋም ለአቅመ ደካሞችና ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን የሚሆን የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር አስረከበ፡፡

 

ትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19ኛን ተጽዕኖ ለመቋቋም ለአቅመ ደካሞችና ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን የሚሆን የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር አስረከበ፡፡

ድጋፉ የምግብ እህል፣የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ወጪ የተሸፈነ ነው ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ( ደ/ር ኢንጅ) ድጋፉን ለአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ኃላፊዎች ያስረከቡ ሲሆን በቀጣይም የሀገር አቀፉን የማዕድ ማጋራት ጥሪ አካል የሆነ ድጋፍ  ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተቀበሉት የወረዳው አስተዳደር ኃላፊዎች ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በችግር ውስጥ ላሉና ለተለዩ 200 አባወራዎች ድጋፉ እንደሚከፋፈል ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ( ደ/ር ኢንጅ)  ከድጋፉ በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን ለማሳካት የትምህር ዘርፉን የ500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቀጣይ ረቡዕ በይፋ እንደሚጀምር የገለፁ ሲሆን በዚህ መርሃ ግብር ላይም ተማሪዎችና መምህራን ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Recent News
Follow Us