News Detail

ዓለም አቀፍ ዜና
Aug 04, 2020 1.2K views

የኮሮና ቫይረስ 1ቢሊየን ተማሪዎች ከቤት እንዲውሉ ማድረጉን ተገለፀ።

የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት በ አለም ደረጃ አንድ ቢሊዬን ተማሪዎች ከ ቤት እንዲውሉ እንዳደረገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የኮሮና ወረርሽኝ አደገኝነት እና ስርጭት ከታወቀ ካለፈዉ ሐምሌ ወር አጋማሽ ወዲህ በዓለማችን በሚጊኙ 160 ሃገራት ዉስጥ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸዉን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታዉቋል።

በ 160 ሃገራት ዉስጥ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ መሆኑም አስታዉቋል።

ይህ ማለት ቢያንስ ወደ 40 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት ትምህርት ቤት ተዘግቶባቸዋል፤ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተረሽ ተናግረዋል።

በየሃገራቱ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት በቁጥጥር ስር መዋሉ ከታወቀና ፤ ስርጭቱ እንዳይባባስ ጥንቃቄዉ የተሟላ ከሆነ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲሄዱ ማድረግ ተቀዳሚዉ ስራ መሆን ይኖርበታል ሲሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አስጠንቅቀዋል።

Recent News
Follow Us