News Detail
Jan 01, 2021
587 views
የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ
ትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣በቴክኖሎጂ፣በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡትን የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ለረቂቅ መመሪያው ግብዓት የሚሆን ሃሳብ ለማሰባሰብ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት በአዳማ ተካሂዷል።
በውይይቱ የተሳተፉት ባለሙያዎችም መመሪያው በውድድር ሂደት ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
ከአዲሱ የትምህርት አደረጃጀትና ሥርዓት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን መመሪያው ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ተጠቅሷል፡፡
ከዚህ ቀደም የዓለም የሳይንስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ከ"ስቴም ፓወር" ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፈጠራ ስራዎች ውድድር ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራቸውን አቅርበው መሸለማቸው ይታወሳል፡፡