News Detail

National News
Aug 11, 2020 1.5K views

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን የነፃ ዝውውር ማስፈፀሚያ መመሪያ ይፋ አደረገ፡፡

የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ በመከሰቱ ተማሪዎች በነፃ እንዲዛወሩ የተወሰነውን ውሳኔ ተክትሎ የወጣው መመሪያ ለሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በመመሪያው እንደተገለፀው የነፃ ዝውውር የሚደረግላቸው በ2012ዓ.ም የ1ኛ ወሰነ ትምህርታቸውን ተከታትለው የወሰዱና ውጤታቸው በሮስተር የተመዘገበ መሆኑ የተረጋገጠላቸው

እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የማታ ተማሪዎች የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚዛወሩ ይሆናል በሁለተኛ ደረጃ ከ 9-12ኛ ክፍል የሚማሩ የማታ ተማሪዎች ደግሞ አንድን ክፍል ለማጠናቀቅ ሦስት ሴሚስተር የሚጠበቅባቸው በመሆኑ የመጀመሪያውን ተርም ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በጀመሩት ክፍል ወደ ሦስተኛ ተርም እንዲሸጋገሩ ተደርጎ የማካካሻ ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

የተማሪ ሪፖርት ካርድን በተመለከተ የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ውጤታቸውን መመዘገብና በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ዓምድ ላይ በኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ወደ ቀጣዩ ክፍል በነፃ ተዛውሯል/ራለች የሚል ተጽፎበት ለተማሪዎች መደረስ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከ8ኛ እና 12 ክፍል በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች በነፃ ወደ ቀጣይ ክፍል እንዲዛወሩ ተደርጎ የማካካሻ ትምህርት እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

Recent News
Follow Us