News Detail

National News
Dec 25, 2025 37 views

ሥራ ፈጣሪነትንና ፈጠራን በማስተማርና በማበረታታት ምሩቃንን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ማሸጋገር እንደሚገባቸው ተመላከተ

ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎችን ሀሳብና ፈጠራ በመደገፍ ምሩቃን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
‎ዩኒቨርስቲዎች በአብዛኛው በማስተማር ስራ ላይ እንደሚያተኩሩ ያነሱት ሚኒስትር ዳኤታው ነገር ግን የሥራ ፈጠራ ሀሳቦችን ማመንጨትና ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን ህይወት መለወጥና ኢኮኖሚውን ማሳደግ እንደሚ ጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
‎ይህ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነትም የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ሀሳቦችን በመደገፍ ክፍተቶች ለመሙላትና የንግድ ፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት እንደሚያስችል ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
‎የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሐሰን ሁሴን (ዶ/ር) ስምምነቱ የፈጠራና ኢኖቬሽን ስራዎችን በማበረታታት ችግሮችን ወደ እድል ለመቀየር እንደሚያስችል ተናግረዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱ ትምህርት ሚኒስቴር የቢዝነስ ቴክኖሎጂ ፣ ኢኖቬሽንና ኢንኩቤሽን ማዕከላት በማቋቋም እያከናወነ የሚገኘውን የሪፎርም ሥራ እንደሚያጠናክረውም የተገለጸ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥራ ፈጠራ ክህሎትን በማስተማርና የፈጠራ ሀሳቦች እንዲጎለብቱ በትኩረት መሥራት ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።
‎የስምምነት ሰነዱ የትምህርት ሚኒስቴርና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ተፈርሟል።
Recent News
Follow Us