News Detail

National News
Sep 05, 2024 1.3K views

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአሜሪካ የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ቻንስለር በዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በጽ/ ቤታቸው አነጋገሩ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ቻንስለሩንና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ አገራችን ዘመናዊ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት ታሪክና መስፋፋት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የረትገር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂና በሌሎችም የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መክረዋል፡፡
ዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ በበኩላቸው የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ከማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ከሌሎችም የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮቸ በትብብርና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
Recent News
Follow Us