News Detail

ዓለም አቀፍ ዜና
Aug 04, 2020 921 views

በጀርመን በኮሮና ምክንያት ት/ቤት ከተዘጋ በኋላ የመጀመርያዎቹ ተማሪዎች ትናንት ወደ መማርያ ክፍላቸው ገብተዋል፡፡

በጀርመን ት/ቤቶች መከፈት የጀመሩ ሲሆን በሰሜን ጀርመን ሜክሌንበርግ ግዛት የሚገኙ ተማሪዎችም ከክረምት እረፍት በኋላ ለሙሉ ሰአት ትምህርት ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ በሀገሪቱ የመጀመርያዎቹ ሆነዋል፡፡

የጀርመን ፌደራል ትምህርት ሚኒስትር አንጃ ካረሊሼክ በትምህርት ቅጥር ግቢ ውስጥ የፊት መሸፈኛ ማስክ ማድረግ አስገዳጅ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በትምህርት ቤቶች ውስጥ መሟላት ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የመጨረሻው ውሳኔ የሚሆነው ግን የክልል መንግስቱ ነው ፡፡

ትምህርት ቤቶች የተወሰኑ ክፍሎችን ሲሰጡ የነበረ ቢሆንም፣ ጥቂቶች ደግሞ በከፊል የተወሰኑ ሰአቶች ለማስተማር ሲሞክሩ የነበረ ቢሆንም በመደበኛነት ሙሉ በሙሉ ሲጀመር ግን ትናንት የመጀመርያው ነው፡፡

በሀምቡርግ ከነገ በስትያ ትምህርት የሚጀመር ሲሆን በበርሊን ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል ተብሏል፡፡

ላይፕዚንግ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝ ምንጭ አይሆኑም ሲል ባጠናው መሰረት ነው ጀርመን ት/ቤቶቿን ሙሉ ለሙሉ ለመክፈት የወሰነችው፡፡

Recent News
Follow Us