Fact Sheets

እውናዊ መረጃዎች

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር አጭር እውናዊ መረጃ

  1. አጭር ታሪክ፡- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የትምህርት ሚኒስትር (ትሚ) በ1935 ዓ.ም ተመሠረተ
  2. አድራሻ ፡- የትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ይገኛል።
  3. የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ እና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተባሉ ሁለት ዘርፎች የተከፈለ ነው።

 

1. አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ በዋነኛነት የቅድመ መደበኛ ፣ የ1ኛ ደረጃ፣ የመካከለኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የሚመራ ሲሆን በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ያሉ የዘርፉ አጫጭር መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።

ሀ. በ2015 የትምህርት ዘመን በሁሉም ክልልችና ከተማ መስተዳድሮች ያሉ የትምህርት ቤቶች ብዛት

በ2015 የትምህርት ዘመን ከ1ኛ-12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ት/ቤቶች በትምህርት ቤት መሻሻል ፖርታል ( sip.moe.gov.et ) መሰረት 56,618 ሲሆኑ ከእነዚህም 11,095 ቅድመ አንደኛ ደረጃ  37,412 የሚሆኑት የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 3,791 ደግሞ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናቸው  ቀሪዎቹ 4320 የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት መስጫ(ABE) ናቸው። 

ለ. በ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ብዛት

በ2015 የትምህርት ዘመን በአንደኛና በመካከለኛ ደረጃ (ከ1ኛ-8ኛ ክፍል) ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ወንድ= 8,708,334 እና ሴት 7,927,109 ተማሪዎች በድምሩ 16,635,443 ሲሆኑ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ደግሞ ወንድ= 1,383,442 እንዲሁም ሴት= 1,446,277 ድምር 2,829,719 ተማሪዎች ናቸው። ይህ መረጃ የትግራይ ክልልን አያካትትም።

ሐ. የመምህራን ብዛት

2015 የትምህርት ዘመን የመምህራን ብዛት፣

  • ቅድመ መደበኛ:- ወ= 9266፣ ሴ= 62705፣ ድ= 71,971
  • ‘O’ ክላስ ወ=7,470 ፣ ሴ=18803 ፣ድ= 26,273  
  • አንደኛ ደረጃ:- ወ= 19,5231፣ ሴ= 162,848 ፣ድ= 358,079
  • መካከለኛ ደረጃ:- ወ=111,687፣ ሴ=42,999፣ድ= 154,686
  • 2ኛ ደረጃ:- ወ=113,125፣ሴ=28,446፣ድ= 141,571 ሲሆን ጠቅላላ ድምር 751,580 ይሆናል።

መ. በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የትኩረት መስኮች የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ አካባቢ ሳይንስ፣ የግልና ማህበራዊ ስሜታዊ እድገት፣ ስነ-ጥበብ፣ ሒሳብ እና ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ናቸው።
  • አንደኛ ደረጃ (1-6ኛ ክፍል) የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ፣ እንግሊዝኛ ቋንቋ፣ አካባቢ ሣይንስ፣ ሒሳብ፣ የግብረ ገብ ትምህርት፣ ሥነ ጥበብ እና ጤናና ሰውነት ማጐልመሻ ትምህርቶች ይሰጣሉ።
  • መካከለኛ ደረጃ (7-8ኛ ክፍል) የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣የፌዴራል የሥራ ቋንቋ፣እንግሊዝኛ ቋንቋ፣አጠቃላይ ሣይንስ፣ ማህበራዊ ሣይንስ፣ የዜግነት ትምህርት፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ጤናና ሰውነት ማጐልመሻ ትምህርት፣ የሥራና የቴክኒክ ትምህርት፣ሒሳብ እና ሥነ ጥበብ ናቸው።
  • ሁለተኛ ደረጃ (ከ9 - 10ኛ ክፍል) የሚሰጡ የጋራ የትምህርት አይነቶች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊ፣ታሪክ፣ የዜግነት ትምህርት፣ ኢኮኖሚክስ፣ የመጀመሪያ ቋንቋ፣ የጤናና ሰውነት ማጐልማሻ ሲሆኑ እንደ አማራጭ ደግሞ የፌዴራለ ቋንቋ፣ የውጭ ቋንቋ፣ ስነ ጥበብ ናቸው።
  • ሁለተኛ ደረጃ (ከ11-12ኛ ክፍል- ተፈጥሮ ሳይንስ) የጋራ የትምህርት አይነቶች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ግብርና ሲሆኑ፣
  • ሁለተኛ ደረጃ (ከ11-12ኛ ክፍል- ማህበራዊ ሳይንስ)፣ እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪክ፣ ኢኮኖሚክስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ናቸው።

ሠ. የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ብዛት

የ10ኛ ክፍል ፈተና ብሄራዊ ፈተና ከቆመ በኋላ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞቸ ቁጥር ከፍ እያለ የመጣ ሲሆነ በ2014 እና 2015 የትምህርት ዓመታት 896,520 እና 845,099 የተፈተኑ ሲሆን በ2015 የትምህርት ዘመን ከተፈተኑት መካከል 50% እና በላይ በማምጣት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት የቻሉት 3.2% ብቻ ናቸው።

 

2. ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ

ሀ. የመምህራን ኮሌጆች ብዛት 

የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች (መትኮ) ዋና ዓላማ ለመምህራን አስፈላጊውን የእውቀት፣ አመለካከት፣ የሙያ ስነባህርያት እና ክህሎቶች በማስታጠቅ እጩ መምህራን የሚጠበቅባቸውን የክፍል / ትምህርት ቤት/ ተግባራት በብቃት ማከናወን እንዲችሉና ሰፊውን ማህበረሰብ እንዲያገለገሉ ያለመ መርሀ ግብር ነው፡፡ በመላ አገሪቱ በአሁኑ ጊዜ 38 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ያሉ ሲሆን እጩ መምህራንን በመምህርነት ሙያ ለ3 አመታት በመደበኛ፣ በክረምት ፣ እና በተከታታይ (በምሽትና ቅዳሜና እሁድ) በዲፕሎማ መርሀ ግብር ያሰለጥናሉ።

ለ. የዩኒቨርስቲዎች ብዛት  

በሀገራችን ያሉ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ3 የትኩረት መስኮች ተከፍለው ለዜጎች አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን፣

  • የምርምር ዩኒቨርስቲዎች በቁጥር 8
  • የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች በቁጥር 17 እና
  • የአጠቃላይ ዩኒቨርስዎች በቁጥር 21 ሲሆኑ አጠቃላይ የመንግስት ዩኒቨስቲዎች 46 ናቸው።
  • በተጨማሪመ በግሉ ዘርፍ ተከፍተው በስራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ኮሌጆች 659 ሲሆኑ ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ 5 ናቸው።

ሐ. የተማሪዎች ብዛት

በ2015 በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቀን፣ በማታ፣ በርቀት እና በኦንላይን መርሃ ግብር ለመማር የተመዘገቡ (በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማስተርስ ዲግሪና በፒኤች ዲ ዲግሪ) ወንድ 317,837 እና ሴት 142,467 በድምሩ 460,304 ናቸው። ይህ አሀዝ በሪሜዲያል ፕሮግራመ የገቡትን እና በትግራይ ክልል ያሉ ዩኒቨርስቲዎችን አያካትትም። ከዚህ በተጨማሪመ በ2015 የትምህርት ዘመን በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች 436,920 ናቸው።

መ. የመምህራን ብዛት