News Detail
Nov 17, 2020
676 views
በዶሃ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ዓለም አቀፍ ት/ቤት በይፋ ተመረቀ።
በዶሃ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ዓለም አቀፍ ት/ቤት በይፋ ተመርቋል፡፡
የቀጠር ትምህርትና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር መሃመድ ቢን አብደልዋህድ አል ሃማዲ እና የሚሲዮናችን መሪ ክብርት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ት/ቤቱን በይፋ መርቀውታል።
የት/ቤቱ መከፈት በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የመለሠ ሲሆን፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በተመጣጣኝ ክፍያ እንዲያስተምሩ፣ ልጆች የአገራቸውን ቋንቋ እና ባህል እንዲያውቁ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የትምህርት ወጪ እና በቋንቋ ምክንያት ልጆቻቸውን ወደ አገር ቤት ለትምህርት መላክን የሚያቃልል ነው ተብሏል።
ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ ሥራውን ሲጀምር ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ሁለተኛ ጀረጃ ትምርት ለማስተማር የሚያስችሉ በቂ የመማሪያ ክፍሎች አሉት።
ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሥራውን በመስከረም 2013 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 2ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።
የቀጠር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ በ 2010 ዓ.ም በዶሃ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መማሪያ የሚሆን የትምህርት ቤት ህንጻ ለመስጠት መፍቀዳቸውን ተከትሎ የተገነባ ትምህርት ቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምንጭ - የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዶሃ