News Detail

ዓለም አቀፍ ዜና
Aug 24, 2020 950 views

ተማሪዎች በኮሮና ምክንያት ከሚደርስባቸው ጉዳት ይልቅ ትምህርት ባለመሄዳቸው የሚደርስባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሲሉ የእንግሊዝ ከፍተኛ የህክምና አማካሪ ተናገሩ፡፡

ህፃናት በበሽታው የመሞት እድላቸው ከሌሎች አንፃር ዝቅተኛ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲይ ህፃናቱ ከትምህርት ቤት በመራቃቸው ግን በረጅም ጊዜ ውስጥ ጉዳት ያስከትልባቸዋል ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ለሚቀጥኩት 9 ወራት የዓለም ስጋት ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት፡፡
በርካታ ህፃናት ቤት በመዋላቸው እየተጎዱ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ የአዕምሮና አካላዊ ጉዳት በረጅም ጊዜ ውስጥ ሊገጥማቸው ይችላል የሚል ሰጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት በሁሉም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች መስከረም ላይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ብሏል፡፡ በስኮትላንድ ደግሞ ትምህርት ቤቶች መከፈት ጀምረዋል፡፡
በኮቪድ 19 ምክንያት ቤታቸው የዋሉ ህፃናት ትምህርት ቤት ከሚውሉት የበለጠ ተጎጂ ናቸው ብለዋል፡፡
ከስጋት ነፃ አማራጭ የለም ያሉት አማካሪው ወላጆችና መምህራንም የትምህርት ቤቶችን መከፈት ጥቅምና ጉዳት ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡

Recent News
Follow Us