News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 02, 2020 582 views

በህብረተሰቡ ተሳትፎ ታሪኩ የተቀየረው ትምህርት ቤት።

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ቲሊሊ ከተማ የሚገኘው ኪሊ መስክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በህብረተሰቡ ተሳትፎ በአዲስ መልክ ተገነባ።

ከዚህ ቀደም ት/ቤቱ ለመማር ማስተማር ሂደቱ አስቸጋሪ እና የማይመጥን ተማሪዎች በፈራረሰ እና በወደቀ፣ በር እና መስኮት በሌለው ፣ ዝናብ እና ፀሀይ በሚፈራረቅበት ክፍል ውስጥ ነበር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት ።

የትምህርት ቤቱ አመራራ ችግሩን ለ አካባቢው ማህበረሰብ ይፋ በማድረግ ማህበረሰቡ ችግሩን ተመልክቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ድጋፍ ማስባሰብ ጀመረ።

አሰሪ ኮሚቴው ህብረተሰቡን ከጎኑ በማድረግ፣ምሁራንን በማማከር፣ባለሀብቶችንም በር በማንኳኳት እና የሚገጥሙ ችግሮችን በመፍታት ወደ ስራ በመግባት ት/ቤቱ በአዲስ መልክ እንዲሰራ አድርጓል።

በዚህም በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ አዲስ እና ለመማር ማስተማሩ ሚመጥኑ 5 ብሎኮች ያሉት 25 መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት ተችሏል።

ይህ ተግባር የማህበረሰብ ተሳትፎ ማህበራዊ ችግርን በጋራ ለመፍታት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ያመላከተ ነው። በእንቅስቃሴው ላይ ለተሳተፉ የማህበረሰብ ክፍሎችም ምስጋና ይገባቸዋል።

Recent News
Follow Us