News Detail
Oct 17, 2025
20 views
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በጊዚያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ተዘዋውረው ተመለከቱ ።
የትምህርት ሚንስትሩ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን በጋምቤላ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እያስገነባቸው ባሉ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ የተቀበላቸውና በጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች በጊዜያዊነት በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ ተማሪዎች የመማር ማስተማር አገልግሎት ያዘጋጃቸውን የተማሪዎች ቤተ-መጽሐፍት፣ የኮምፒውተር ክፍል፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ እና የመኝታ ክፍሎች እና ሌሎችንም አይተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ሚንስትሩ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙትን ስማርት እና ኮንፈረንስ ክፍሎች እንዲሁም የኬሚስትሪና የማይክሮ ባዮሎጂ ቤተ-ሙከራዎችን የጎበኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ጥሩ መሻሻሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርታቸው የላቁና ብቁ ተወዳሪ እንዲሁም ወደፊት የሀገር መሪ የሚሆኑ ልጆችን ለማፍራት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባ ሲሆን በአምስቱ በቅርቡ የመማር ማስተማር ሥራ የሚጀመር ይሆናል።