News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 29, 2020 491 views

ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡

በ ትምህርት ቤቶቹ ላይ ውሳኔ የተላለፈው ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡

ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት( ትምህርት ሚኒስቴር) ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ትምህርት ቤቶቹ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸው ተገልጿል፡፡

Recent News
Follow Us