News Detail
Oct 23, 2025
200 views
ማስታወቂያ
የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምህርነት ለተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
የጽሁፍ ፈተና በተመረጡ 18 ዩኒቨርስቲዎች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ተፈታኝ መምህራን ጥቅምት 17/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ከታች ከተዘረዘሩት የዩኒቨርስቲ አማራጮች በሚቀርባችሁ ዩኒቨርስቲ በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ በፊት ከነበረው ስም ዝርዝር በተጨማሪ እንደ አዲስ የተካተታችሁ ስላላችሁ ስማችሁን በድጋሚ በ(https://sbs.moe.gov.et/career/check-status) በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑንን እየገለፅን በተጨማሪም የሚቀርባችሁን የፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) መርጣችሁ እንድታስገቡ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፤ ማንኛውም መምህር ለፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ ሲመጣ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መቅረበ ይኖርበታል።
የፈተና መስጫ ማዕከላት (Exam center)
1. ወሎ ዩኒቨርስቲ
2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
4. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
7. ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ
8. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
9. ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ
10. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
11. ዋቻም ዩኒቨርሲቲ
12. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
13. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
14. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
15. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
16. አክሱም ዩኒቨርሲቲ
17. ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
18. ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ