News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Apr 12, 2025 16 views

ዩኒቨርሲቲዎች በትክክል የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆን ከመንደር አስተሳሰብ ወጥተው ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ማፍራት ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ አሳሰቡ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከጅንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ በመወጣት በአለም ሁኔታ እውነተኛ ውይይት የሚደረግባቸውና ለማህበረሰቡ አቅጣጫ የሚሰጡ እውቀቶች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ለእውነትና እውቀት የሚሰጡት ትኩረት አናሳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ተማሪዎች ክፍል ከሚማሩት ትምህርት በተጨማሪ አለም አቀፍና ሀገራዊ ሁኔታዎችን እንዲያውቁና ለዛ እንዲዘጋጁ ምሁራዊ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፤
ስለሆነም ዩኒቨርሲቲዎች በትክክል ልጆች የሚማሩባቸው የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆን ከመንደር አስተሳሰብ ወጥተው ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ማፍራት ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው የዛሬው ውይይት ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር የሪፎርም ተግባራትን እንዴት እያስኬዱ ነው የሚለውን ለመለየት ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አክለውም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ራሱን የሚችል፣ ሀገሩን የሚጠቅም ተወዳዳሪ የሆነ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ዩኒቨርሲቲዎች በውጤት መለካት ይኖርባቸዋል፤ ለዚህም ሚኒስቴሩ ተጠያቂነት የሚያስከትል ስምምነት ከዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር መፈራረሙን ጠቅሰዋል።
Recent News
Follow Us