News Detail
Feb 25, 2025
38 views
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከፊንላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ጋር ተወይተዋል፡፡
በዚሁ ጊዜ ፊንላንድ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች በጥራትና በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድርግ የሄደችበት መንገድ በሞዴልነት የሚወሰድ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል፡፡
አክለውም በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በሪፎርሙ የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡
በዚህም በትምህርት ዘርፉ የሪፎርም ሥራዎች ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት አጋር ድርጅቶች ገንዘባቸው በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን በሚያረጋግጥ እና የትምህርት ሚኒስቴርን የሪፎርም እቅዶች ለማሳካት በሚያስችል መልኩ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው በትምህርቱ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በርካታ ሥራዎችን በትብብር መስራታቸውን አንስተው ይህንን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
በተለይም በመምህራን የአቅም ግንባታ፣ ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት፣በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በሌሎችም የትምህርት ዘርፎች በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይት የሚደረጉ ማናቸውም ድጋፎች በትክክል የህጻናትን የመማር ሁኔታ በሚያመቻቹና ጥራትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሆኑ ተስማምተዋል፡፡