News Detail
Jan 26, 2025
169 views
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ በተዘጋጀው የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በውይይቱ መክፈቻ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት ቁልፍ መልእክት የትምህርት ስርዓቱ ፍትሃዊ፣ አካታች፣ ተደራሽነት ያለውና ችግር ፈቺ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለውና እየተሻሻለ የሚሄድ የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓት የመዘርጋት፣ ስታንደርዶችን የማውጣትና ተግባራዊነታቸውን የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።
በዚህም ዜጎች የሀገሪቱን ልማትና ዕድገት ለማሳለጥ የሚያስችል ዕውቀት፤ ክህሎት እና አመለካከት ይዘው እንዲወጡና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርዶች የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።
የትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ መመሪያው ከጸደቀ በኋላ በአዲሱ የስልጠና ጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ መሠረት የሚመዘኑ መሆኑ ተጠቁሟል