News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 10, 2024 182 views

ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ስኬታማ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲኖር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

የፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የትምህርት ትብብር የሉዑካን ቡድን በትምህርት ሚኒስቴር ጉብኝት አድርጓል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ተወካይና የአስተደደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የልዑካን ቡድኑ ከከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲኖር እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር እንዲችሉ በወጣው የህግ ማዕቀፍ መሰረትም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ በደንብ እንዲደራጅ በህግ መደንገጉንም ዶክተር ሰለሞን ተናግረዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝነት ለማጠናከር የትምህርት ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከፈረንሳይ ዩኒቨርስቲዎች ጋር የጀመረው የቴክኒክ ድጋፍና የልምድ ልውውጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ከዓለም አቀፍ ደረጃና የገበያ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ስርዓተ ትምህርት እንዲኖራቸው ለማስቻል እና ወጥነት ያለው የትምህርት ደረጃን ለማረጋገጥ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡
በፈረንሳይ ዩኒቨርስቲዎችና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል በትምህርት ጥራት ፣ በቴክኒክ ልምድና አቅም ግንባታና በሌሎችም ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ትብብር እንዲሁም ጠንካራ ትስስር እንዲኖር እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የትምሀርት ትብብር የልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸው የፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የትምህርት ትብብር ከአፍሪካ ትምህርት ተቋማት ጋር በአቅም ግንባታ ፣በልምድ ልውውጥ፣ በተማሪዎችና መምህራን እንቅስቃሴ እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ በሆኑ የትምህርት ልማት ስራዎች በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
የፈረንሳይ ዩኒቨርስቲዎችና ትምሀርት ተቋማት በቴክኒክ ፣ በአቅም ግንባታ ፣ በቴክኖሎጂ፣ እና በትምህርት ጥራት ማሻሻያ። ስራዎችና በሌሎችም ያላቸውን እውቀት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን ለማጋራትና ለማካፈል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
Recent News
Follow Us