News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 02, 2024 131 views

የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በዓል ህብረብሄራዊ አንድነታችንንና የጋራ እሴቶቻችንን የምናጠናክርበት በዓል መሆኑ ተገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አክብረዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ህዳር 29 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሀገራችንን አንድነት፣ ብዝሀነትና ሕብረብሄራዊነታችንን የምናጠናክርበት ዕለት ነው ብለዋል።
ህብረብሄራዊነታችንና ብዝሃነታችንን አብረን በመኖር በተግባር የምናውቀው እውነታ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ይበልጥ በማጠናከር ልናስቀጥለው የሚገባ የጋራ እሴት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዕለቱን ስናከብር ስለአገር ግንባታና ስለ አብሮነታችን በግልጽ በመወያየትና በማጎልበት ሊሆን እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው ዴሞክራሲ የፌዴራዝም መገለጫ መሆኑን ጠቁመው የዴሞክራሲ ባህል አለመጎልበት የፌዴራል ስርዓቱ ዋነኛ ፈተና መሆኑን ተናግረዋል።
የሚስተዋሉ አንዳንድ ክፍትቶቻችንም በውይይትና በሰከነ መንፈስ መፍታት እንደሚገባ ጠቁመው ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በግልጽ በመነጋገር መፍትሄ ማፍለቅ ብሎም በሄራዊ አንድነተን በማጎልበት ጠንካራ አገር መመሥረት እንደሚገባም የሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊው
አመልክተዋል።
“ሀገራዊ መግባባት ለብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚሁ በዓል ላይ የህብረ ብሄራዊ ፌዴራል ስርዓት አወቃቀር በሚል ርዕስ በአቶ ዑመር ኢማም ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
Recent News
Follow Us