News Detail
Nov 26, 2024
258 views
በትምህርት ቤቶች መካከል እየተካሄደ ያለው የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድር ቀጥሎ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በአፋር ክልል ትምህርት ቤቶችም በድምቀት ተጀመሯል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግን በተለያዩ ክልሎች እያስጀመረ ይገኛል።
በዚህም የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በአፋር ክልል ትምህርት ቤቶች በድምቀት ተጀመሯል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ስፖርት ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ሀገሪቱ ክፍሎች እንደ ተማሪዎቹ ዕድሜ አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገት እንዲሁም የክፍል ደረጃ ታሳቢ ያደረገ ከትምህርት ሰዓት ውጪ ስፖርታዊ ውድድሮችንና ፌስቲቫሎችን ለማስፋት የሚያስችል የትምህርት ቤቶች ሊግ ስፖርታዊ ውድድር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
ይህም ተማሪዎች ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲያመጡ ብሎም ለሀገራችን ተተኪ ስፖርተኞችን ለማውጣት ዘርፈ ብዙ ጠቀሚታዎች ይኖሩታል ተብሎ ይገመታል፡፡
በዚህም የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድሮች በምስራቅ ቀጣና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች በቮሊቦል፣ እግር ኳስ፣ እጅ ኳስ፣ ጂምናስቲክስ፣ ጠረዼዛ ቴኒስ፣ ቼስ እና በባህል ስፖርቶች ውድድሮች በትምህርት ቤት ደረጃ በድምቀት በማስጀመር ውድድሮች መካሄድ ጀምረዋል።
በሌላ በኩል በአፋር ክልል በዞን 2 በራህሌና በዞን 3 ዱሌቻ ወረዳዎች የሚገኘኙ ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ ስፖርት ውድድር የጀመሩ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ክልሎች የትምህርት ቤቶችን ስፖርት ውድድር እንደሚጀምሩና እንደሚያስቀጥሉ ይጠበቃል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024