News Detail
Oct 24, 2024
1.6K views
የትምህርት ሚኒስቴር በ’GEQIP-E) የተገዙ 1000 የሚጠጉ ሞተር ብስክሌቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ጥራት ማሻሻል ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) በጀት የተገዙ ሞተር ብስክሌቶች ለሁሉም ክልሎችና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አከፋፍሏል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት ድጋፉ የትምህርትን ጥራትና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግና የመማር ማስተማር ሥራውን ለማሳለጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ሞተር ብስክሌቶቹ የክልሎችን የወረዳዎችና የትምህርት ቤቶች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የትምህርቱን ስራ በተጨባጭ ለመደገፍ የተከፋፈሉ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስረድተዋል፡፡ የሞተር ብስክሌቶቹ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በአለም ባንክና የልማት አጋሮች የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ መሆናቸውን ጠቁመው ልማት አጋሮቹ የዘርፉን ክፍተት በማየት ላደረጉት ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ሞተር ብስክሌቶቹ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮዎች ክትትል ሊያርጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላሂ አብዲ በክልሉ የትራስፖርት እጥረት መኖሩን ጠቅሰው ሞተር ብስክሌቶቹ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ወደ ትምህርት ቤቶች ወርደው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንደሚያግዙ ተናገረዋል፡፡
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ አደም በበኩላቸው አብዛኛ የክልሉ አካል ገጠር በመሆኑ ሞተር ብስክሌቶቹ ወረዳንና ትምህርት ቤቶችን ለማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከሦስት ወራት በፊት በአጠቃላይ ጥራት ማሻሻል ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) በጀት የተገዙ 26 ሀርድ ቶፕ ላንድክሩዘር እንዲሁም 26 ደብል ጋቢና ፒክ አፕ በድምሩ 52 ተሸከርካሪዎችንም ለክልሎች ማከፋፈሉ ይታወሳል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024