News Detail
Oct 23, 2024
1.7K views
ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፓርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም መስኮች ያላትን የትብብርና የወዳጅነት ግንኙነት አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
የአገራቸው መንግስት በትምህርትና በባህል ዘርፍ ያለውን ወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት በማስፋት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል የማሳደግ ፍላጎት እንዳለውም ሚኒስትሩ ኑኖ ሳምፓዮ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በፖርቹጋል መንግስታት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ከሚኒስትሩ ጋር በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎችም በሁለቱ አገራት መካከል የአካዳሚክ ትብብሮች በሚጠናከሩበትና አሁን ያለው ግንኙነትን በሚሰፋበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሙዚየም እያቋቋመ በመሆኑ ፖርቹጋል በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎና ታሪክ ልታኖር እንደሚገባም ክቡር ሚኒስተሩ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊዛ ፋራጋሶ በበኩላቸው አገራቸው የፖርቸቹጋል ብሄራዊ ቀንን ምክንያት በማድድግ በያሬድ የመዚቃ ትምህርት ቤት የባህል ትርኢት የማቅረብ ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024