News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jul 18, 2024 1K views

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ተፈታኞችን አበረታቱ።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በአብርሆት ቤተመጻህፍትና በመነን ትምህርት ቤት መፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት የፈተና እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል። ተፈታኝ ተማሪዎችንም አበረታተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ከሐምሌ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን በመፈተን ማስጀምሩ ይታወሳል። ይሄው አገር አቀፍ ፈተና ሁለተኛውን ዙር ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የቀጠለ ሲሆን በትግራይ ክልል በአሮጌው ካሪኩለም የሚፈተኑ ተማሪዎች በነገው እለት ሲያጠናቀቁ የሌሎች ክልሎች ተፈታኞች በዛሬው እለት የሚጨርሱ ይሆናል።
ክብርት ወ/ሮ አየለች ጉብኝቱን ባደረጉት ወቅት ለፈተናው የተደረገው ዘርፈብዙ ዝግጅትና ውጤት የተቋማት ትብብር የፈጠረው ውጤታማነት መሆኑን ገልጸዋል።
Recent News
Follow Us