News Detail
Feb 09, 2024
847 views
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናና ውይይት እካሄዱ፡፡
ከ”እዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ መልዕክት እንደ ሀገር በተዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የውይይቱ አላማ ሰራተኛው በሀገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የሰላም ሁኔታ ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።
ውይይቱ በመጀመርያ ቀን ውሎው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፣ እያጋጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራአስፈፃሚ ኤባ ሚጅና(ፒኤችዲ) ቀርቧል።
በቀረበው ሰነድ መነሻ በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የአጠቃለይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴና በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኮራ ጡሹኔ መሪነት ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ውይይቱ ዛሬም አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርእስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024