News Detail
Jan 18, 2024
822 views
“አድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ’’ በሚል መሪ መልዕክት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰላምና ሀገር ግንባታ ፎረም አገር አቀፍ ንቅናቄ ተጀመረ።
"አድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ መልዕክት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚካሄደው አገር አቀፍ የሠላም እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ንቅናቄ የትምህርት ማህበረሰቡን አበርክቶ ለማሣደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የንቅናቄው መጀመርን አስመልክቶ የሰላም ሚኒስቴርና የትምህርት ሚኒስቴር በጋራ መግለጫ የሰጡ ሲሆን የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ከይረዲን ተዘራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ተግባራቸው ጎን ለጎን በሰላምና ሀገረ መንግስት ግንባታ ጉዳዮች ላይ ሚናቸውን ሊያሣድጉ ይገባል ብለዋል።
ክቡር ዶ/ር ከይረዲን በመግለጫቸው የአድዋን ድል ለድል ያበቃው የመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ነው ያሉ ሲሆን ለዘላቂ ሰላማችን መስፈን የእያንዳንዳችን ድርሻ ወሳኝነት አለው ብለዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ኩራ ጡሹኔ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብዝሃነትን የተላበሱና የተለያዩ መስተጋብሮችን የሚያስተናግዱ በመሆኑ በሠላምና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ሚናቸው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል ።
ሚኒስትር ዲኤታው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራ ውጤታማ የሚሆነው ሰላም ሲኖር ነው ያሉ ሲሆን ትንሿ ኢትዮጵያ እንደመሆናቸው መጠን በሰላምና በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ መስራት ስላለባቸው ነው የዚህ ንቅናቄ ባለቤት የሆኑት ብለዋል፡፡
ከአድዋ ድል የምንማረው ትልቁን ስዕል ማየት ነው ያሉት አቶ ኮራ የአድዋን መንፈስ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማምጣት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
ሠላምና ሀገረ መንግስት ግንባታ የብዙ አካላት አስተዋጽአዖና ድርሻ በመሆኑ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የድርሻውን እንደሚወጣም ሚኒስቴር ድኤታው አያይዘው ገልጸዋል የንቅናቄ መድረኩ ማጠቃለያ መርሃግብር የካቲት 21/2016 በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን ተማሪዎች እና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በሀገራዊ ዕሴቶች፣በሀገራዊ ማንነቶች እና በብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ውይይትና ምክክር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024