News Detail
Mar 13, 2023
2.6K views
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ፡፡
መጋቢት 4 /2015ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዓመት መጨረሻ በሚሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ደያ ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በስነ-ልቦና የማዘጋጀት ስራ እየሰራ እንዳለም ም/ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ 62 የትምህርት ክፍሎች የማሰልጠኛ ማኑዋሎችን አዘጋጅተው ለተማሪዎቻቸው ስልጠና በመስጠት ላይም እንደሆነም ዶ/ር ሙላቱ አክለዋል።
ለተማሪዎችም በትምህርት መስኩ ማወቅ የሚገባቸውን አበይት ነጥቦች ተዘጋጅተው ዝግጅት እንዲያደርጉባቸው ተደራሽ መደረጉንም ተናግረዋል።
ተማሪዎቹም ፈተናውን እንዲለማመዱና የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው የተለያዩ ሞዴል ፈተናዎች ተዘጋጅተው እየተሰጡ እንዳሉም ም/ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡
በፈተናው ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር ከማድረግ አንፃር ፈተናዎችን በኮምፒዩተር የታገዘ ለማድረግ ሶፍት ዌር የማልማትና ግብዓቶችን የሟሟላት ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡
የመውጫ ፈተና በሀገራችን አዲስ አይደለም ያሉት ም/ፕሬዚዳንቱ የህግና ጤና ተማሪዎችን ከዚህ በፊት አስፈትነው መልካም ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው እሱን እንደ ልምድ በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024