News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Mar 07, 2023 2K views

“ጠንክረን በተማሪዎቹ ላይ በመስራታችን ለተከታታይ አስር ዓመታት በውጤታማነት መዝለቅ ችለናል” የወላይታ ሊቃ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ማቱሳላህ፡፡

የወላይታ ሊቃ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር አቶ ማቱሳላህ ጎና ጠንክረን ተማሪዎች ላይ በመስራታችን ባለፉት አስር ዓመታት በ12ኛ ክፍል ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ በማስገባት በውጤታማነት መዝለቅ መቻላቸውን ገለፁ፡፡
የወላይታ ልማት ማህበር በ2000 ዓ.ም ትምህርት ቤቱን በመመስረት ከ5ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ስራውን በመጀመር የመጀመሪያዎቹን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2005 ዓ.ም ማስፈተኑን ርእሰ መምህሩ ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቱም ለአስር ዓመታት ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ያስገባ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዚህ ትምህርት ቤት የተማሩ ተማሪዎቹም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት በመረጡት ዘርፍ ትምህርታቸውን መከታተላቸውም ተገልጿል።
ትምህርት ቤቱ ላመጣው የላቀ ውጤት የመምህራን እና ተማሪዎች ለትምህርት የሰጡት ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑ መሆኑንም ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል።
ለተማሪዎችም ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የማደሪያ፣ የምግብ ፣ የህክምና ወጪ በወላይታ ልማት ማህበር በመሟላቱ ምቹ የትምህርት ሁኔታ መፍጠር መቻሉም ተገልጿል።
በመጨረሻም ትምህርት ቤቱ ባለበት የውጤታማነት ደረጃ እንዲቀጥል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ማቱሳለህ ተናግረዋል፡፡
Recent News
Follow Us