News Detail
Mar 01, 2023
2.2K views
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ፒኤችዲ)በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እጅግ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችንና ትምህርት ቤቶችን ሸለሙ
በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 273 ተማሪዎች ስኮላር ሺኘ እንደተመቻቸላቸው ገለጸዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድት በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እና 20 ትምህርት ቤቶች እውቅና ሽልማት ሰጥተዋል።
በእውቅና መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን አበረታትተዋል።
ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው የላቀ አድማጭ እና አስቀማጭ ስለሆናችሁ መምህራኖቻችሁ ያስተሟሯችሁን በትክክል ማየት ችላችኋል ያሉ ሲሆን ይህን ወደ እውቀት መቀየር ይጠበቅባችኋልም ብለዋል።
ተማሪዎች በቀጣይ በሚኖራቸው የትምህርት ቆይታ እውቀትን ብቻ ሳይሆን ጥበብን አብዝተው መፈለግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀው በተለይ ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁም ብለዋል።
በመጨረሻም ለ 273 የላቀ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በማብሰር ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም አሳስበዋ
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024