News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Feb 12, 2023 18.8K views

የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተናን 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

ስለሆነም ተማሪዎች ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደባችሁበትን ተቋም ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:  https://result.ethernet.edu.et 

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ

 result.ethernet.edu.et   ላይ በመግባት Complaint

 የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡   

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር

Recent News
Follow Us